ይህ ትምህርት ለወንድ፥ ለሴት ላገቡት፥ ወይም ወላጆች በክርስቶስ ተጣብቀው ለመኖር የሚያስችላቸውን መሰረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የሚያስምር የመልመጃ መጽሐፍ ነው።
አማርኛ የደቀመዝሙርነት ትምህርቶች
የስልጠና ቪዲዮዎች
መጋቢ ክሬግ ለመጋቢዎች እና አማኞች ሁሉ እግዚአብሔር ደቀመዝሙርነትን አስመልክቶ የሰጠው ማስተንቀቂያና ማበረታቻ አካፍሏል። በዚህ ትምህርት ደቀመዝሙርነት ምን ማለት እንደሆነ እና ኢየሱስ ለቤተክርስቲያኑ የሰጠውን ተልእኮ መፈፀም ለምን መሰረታዊ ጉዳይ እንደሆነ ግልጽ የሆነ ራዕይ ትሰንቃላችሁ።
የፒዲኤፍ ትምህርቶች

የመጋቢነት ጥያቄዎች
እነዚህ ጥያቄዎች መሪዎችን ለመገምገምና እና የደቀመዝሙርነት አገልግሎታቸው እንዴት እየተከናወነ እንደሆነ ለመለካት ይረዳቸዋል። ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጡት መልስ ደቀ መዛሙርት ማድረግ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን እና እነሱን የማፍራት ሂደቱ እየተተገበረ መሆኑ ለአማኞች ግልጽ መሆኑን ያሳያል።

ደቀመዝሙርነት ራዕይ እና ሥልት ይፈልጋል
ይህ ትምርት የተጻፈበት ዋና ዓላማ እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔርን ልጆች ደቀ መዝሙር በማድረጉ ሂደት ደቀመዝሙርነት ምን እንደሆነ እና እንዴት መደረግ እንዳለበት ግልጽ ራዕይ፥ ስልት እና ቅድሚያ መስጠት ያለባት ጉዳይ መሆኑን የሚያሳይ መሳሪያ ነው። በቤተክርስቲያንህ ውስጥ ደቀመዝሙርነትን ተግባራዊ ለማድረግ ይህ መረጃ ጠቃሚ ሆኖ ታገኘዋለህ ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

የክርስቲያን መሰረታዊ ትምህርቶች
በድነት ጊዜ የተቀበልነው ትልቁ ስጦታ ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ግንኙነት ማድረግ የሚያስችል መተማመን ማግኘታችን ነው። ደቀመዝሙርነት ከክርስቶስ ጋር እንዴት አንድ መሆን እንደሚቻል እና እርሱን የሚያከብር ህይወት እንዴት ለመኖር እንደምንችል የምንማርበት የእግዚአብሔር ዕቅድ ነው። ይህ ዕለታዊ የግል የጥሞና ጊዜ መለማመጃ መጽሐፍ ሁሉም አማኞች ሊማሩት ስለሚገባቸው መሰረታዊ የክርስትና እምነት ጠቃሚ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶችን ያሳያል። ኢየሱስ ክርስቶስ የቆምንበት ዓለታችን ነው ነገር ግን የአንድ ሰው መንፈሳዊ መሠረት ደካማ ከሆነ ይህ በሁሉም የሕይወታቸው ዘርፍ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል። ይህ ንድፍ ደቀ መዛሙርት ለሚሆኑ ወይም ሌሎችን ደቀመዝሙር ለሚያደርጉ ጥሩ መሣሪያ ነው።

ጋብቻ አገልግሎት ነው
ይህ 5 ተከታታይ መጽሃፍ የእግዚአብሔርን የጋብቻ አላማዎች በጥልቀት ይዳስሳል፣የባልና ሚስትን ሚና ግልፅ ያደርጋል፣እግዚአብሔር ለትዳር ያሰበውን በረከቶች ይዳስሳል፣እና ባለትዳሮች እንዴት እርስ በርሳቸው ማገልገል እንዳለባቸው የተወሰኑ ምሳሌዎችን ይሰጣል። ይህ ተከታታይ ትምህርት አዲስ ለተጋቡ ጥንዶችም የሚጠቅም ነው፣ ቀድሞውንም ጠንካራ ትዳርን ለማጠናከር፣ የምክር መስጫ እንዲሁም ሌሎችን ወይም ትናንሽ ቡድኖችን ደቀ መዝሙር ለማድረግ የሚረዳ መሳሪያ ነው።

ወላጅነት አገልግሎት ነው
ይህ 4 ተከታታይ መጽሐፍ ልጆች ማደግ በሚገባቸው መንገድ በፍቅር፥ በእንክብካቤና በምገባ እንዲያሳድጉ ወላጆች በእግዚአብሔር የተሰጣቸውን የወላጅነት ሚናዎች ምን እንደሆኑ በጥልቀት ይዳስሳሉ። መልካም ምሳሌነት ያልነበራቸው ወላጆች ለማሰልጠን እና ለእግዚአብሔር ፈቃድ እና የወላጅነት ዓላማ ግልጽ የሆኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያዎችን እና እውነቶችን በማቅረብ ይረዳል። ይህ ተከታታይ ትምርት ልጆች ጎልማሳ እስኪሆኑ ድረስ የምናስተምራቸውን የትምርት ዕቅድ ቀርባል።

ይቅርታ እና ዕርቅ
መጽሐፍ ቅዱሳዊ የይቅርታ መርሆችን እና የተበላሹ ግንኙነቶችን የማስታረቅ እርምጃዎችን የሚዘረዝር ባለ 14 ገጽ የመልመጃ መጽሐፍ ሲሆን ለግል ጥናት ወይም አማካሪ ሆኖ ለማገልገል የሚረዳ ጥሩ መሣሪያ ነው።
